Filtrar por género

The Ethio Balkan Show

The Ethio Balkan Show

Tatek Mamecha

ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮች! ይህ በተከታታይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ በተለይም ኢትዮጵያውያን ሊያደምጡት፥ ሊያካፍሉት እንዲሁም ሊነጋግሩበት ይጠቅማል ብለን የምናምንባቸውን ጉዳዮች የምናካፍልበት ፓድካስት ነው። እያዘጋጀሁ የማቀርብላችሁም እኔ ታጠቅ ወንድሙ ማመጫ ነኝ። ፕሮግራማችንን ዳውንሎድ አድርጋችሁ ስለምታደምጡን በጣም እናመሰግናልን።

4 - ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm)
0:00 / 0:00
1x
  • 4 - ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm)

    ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm)

    ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮቼ! እንኳን ወደ ኢትዮባልካን ፖድካስት በሰላም መጣችሁ።

    በዛሬው ፕሮግራማችን የዩጎዝላቪያ ፅንፈኛ የብሄር ፖለቲከኞች ስትራተጂና አካሄድ፥ መሰረታዊ ፀባያትና አላማችንን ያሳካልናል ብለው ከተጠቀሟቸው ዘዴዎች መካከል ዋና ዋናዎቹን እንመለከታለን።

    ሃሃ፥ Modus operandi ነው ዛሬ baby!

    ይሄንንም ከሌሎች ሃገራት ታሪኮች እያጣቀስኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

    ላዛም ነው እነ ሩዋንዳ፥ ናዚ ጀርመኒ ና ሌሎችም መጠቃሳቸው አይቀርም።

    የዛሬውን ፕሮግራም በጣም ግልፅ በሆነ ምክንያት እንደምትወዱት እርግጠኛ ንኝ።

    በዚህ ፕሮግራም ከተካተቱት ዋና ዋና ጭብጦች ምካከል የሚከተሉት ከነ ምሳሌያቸው ቀርበዋል።

    የተጠቂነት ስሜትንና ጥላቻን ማስፋፋት በዩጎዝላቪያ ተቋማቶች ቅቡልነት እንዳይኖራቸውና ስርአት አልበኝነትም እንዲሰፍን ማድረግ ከውስጥ የማፅዳት ዘመቻ አብዛኛውን ህዝብ የተገዳጅ ደጋፊ ማድረግ ወይም ዝም እንዲል ማስገደድ እየተደረጉ ያሉ ወንጀሎችንና የሰብአዊ ቀውሶችን መካድ ወይም አለማመን (creating a scenario of plausible deniability) ለአማራጭ ሀሳቦችና ሁሉን አቀፍ ለሆኑ ድርድሮች በርን ዝግ ማድረግ የብሔር ቅራኔዎችን ወደ ሃይማኖት ቅራኔነት ወይም ሌላ የቅራኔ መስኮችን ፈልጎ ወደዛ ማስፋት ነው እና ሌሎችም

    Listen to yourself while listening to this program.

    Enjoy.

    Wed, 30 Oct 2019 - 40min
  • 3 - ጽንፈኞች ጽንፈኞችን አዋለዱ: ተቋማትንም በጋራ አመከኑ የብሄር ፖለቲካውም ከሀይማኖት ልዩነቶች ጋር እንዲዛመድ ሆነ

    እነሆ ኢትዮባልካን ክፍል 3

    የሰርብ ጽንፈኞች የሌሎች ብሄር ጽንፈኞችን አዋለዱ;

    ተቋማትንም በጋራ አመከኑ

    የብሄር ፖለቲካውም ከሀይማኖት ልዩነቶች ጋር እንዲዛመድ ሆነ;

    ዩጎዝላቪያውያንም መግቢያ መውጫው ጠፋቸው::

    ኢትዮባልካንን ያድምጡ: ይከታተሉ: ያካፍሉ

    Tue, 15 Oct 2019 - 28min
  • 2 - የታላቁ መሪ ማለፍና የፅንፍ ፖለቲካ ጂኒ ከሳጥኗ መውጣት

    እነሆ Ethiobalkan Episode II.

    ጤና ይስጥልኝ ፥ ጤና ይስጥልኝ ፥ ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮቼ!

    በክፍል አንድ ፕሮግራማችን በአንድ አገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት እንዴት ማንም ሳይፈልገው ይቀሰቀሳል? በሚል ጥያቄ ጀምረን የዛሬ 27 አመት ገደማ የዩጎዝላቪያ አብዛኛው ህዝብ ሳይፈልገውና ሳያስበው አሸናፊ ወዳልተገኘለት የለየለት ጦርነት ሃገሪቷ ልትገባ እንደቻለች፥ አልፎም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ታይቶ የማያውቅ እልቂት፥የሰዎች ጭካኔ፥የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት በሰፊው እንደተካሔደ፥ ዩጎዝላቪያም እንደ ሃገር መቆም እንደተሳናትና ልትፈርስ እንደቻለች አንስተን ነበር።

    በዚያ ወደ 11 ዓመት በፈጀ ተከታታይና የተወሳሰበ ግጭትም ወደ 2መቶ ሺህ (በአብዛኛው ሰላማዊ ሰዎች) በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲሞቱ፥ ብዙዎችም ደብዛቸው እንዲጠፋ እንደተፈረደባቸው። ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿም እስከዛሬ ላልተቋጨ ስደት እንደተዳረጉም አንስተን ነበር።

    ታድያ ሁኔታውን ከስረመሰረቱ ለመረዳት ያስችለን ዘንድም የዩጎዝላቪያን የቀድሞ ታሪክ፥ የፌደሬሽኑን አመሰራረት፥ አጠቃላይ የህዝቡንና በውስጧ ተዋህደው የሚኖሩትን የተለያዩ ብሄረሰቦች በጨረፍታ ከዳሰስን በሗላ የማርሻል ቲቶን ከዚህ አለም በሞት መለየት አውስተን ነበር ያቆምነው።

    ታዲያ በዚያው ክፍልም የባልካኑን ቀውስ እንዳቀርብላችሁ ምን እንደገፋፋኝም ጠቅሼ ነበር። በክፍል አንድ እንዳነሳነው የቀድሞዋ ዩጎዝላቭያ እንደዚያ ልይቶላት ከመፍረሷ በፊት የነበሩት የሃገሪቷ አጣቃላይ ሁኔታዎች፥ የፖለቲካ ንትርክና እቅጣጫ ማጣት፥ አነስተኛም ቢሆን እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶችና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ከእያንዳንዷ የሃገራችን የወቅቱ ሁኔታ ጋር በአብዛኛው ተመሳሳይነት እንዳላቸው፥

    ይህም ለረጅም ጊዜ ሲያሳስበኝ እንደቆየ፥ ሆኖም ከቀደምት ታሪኮች የሚማር ብልህ ነው እንደሚባለው የባልካኑን ቀውስ እንዲሁም ሌሎችን በመመርመር በግዜ ከተማርንባቸው የወቅቱን የሃገራችንን ሁኔታና ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ብዙ በአሁኑ ግዜም እያየናችው ያሉ ተመሳሳይ ምልክቶች ወደ አይቀሬና መጥፎ እጣ ፈንታነት ከመለወጣቸው በፊት ለማመላከት ይረዳል ብዬ በማመኔ እንደሆነ አንስቼላችሁ ነበር።

    በዚሁ ስሜትና አላማ ነው እንግዲህ ክፍል ሁለት ኢትዮባልካን ፕሮግራምን የማቀርብላችሁ።

    በዚህ ክፍል ከማርሻል ቲቶ ሞት በሗላ የነበረችውን ዩጎዝላቪያን እያየን በዚያውም ለዩጎዝላቪያ ግብአተ መሬት መብቃት እንዲሁም ለተከሰተው ከፍተኛ የሰብዐዊ ቀውስ፥ የህዝብ እልቂትና ስቃይ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ዋና ተዋናዮችንና ገፊ ተግዳሮቶችን እንቃኛለን።

    አስተያየት ወይም ምክር ካላችሁ ይህ ፓድካስት በfacebook, anchor podcast, google podcast, spotify, radio public, breaker audio, youtube እና በSoundcloud ላይም ስለምታገኙት በአስተያየት መስጫቸው ላይ ሃሳብዎን ቢያሰፍሩ በጣም ደስ ይለናል።

    Mon, 14 Oct 2019 - 35min
  • 1 - የመጨረሻው መጀመሪያ?

    የዛሬ 27 አመት ገደማ የዩጎዝላቪያ ተወዳጅ ሙዚቀኞችና የስነ ጥበብ ባለሙያዎች በሚያዘጋጁት የሰላም ኮንሰርት የሚታደሙ ሁሉ በአንድ ነገር እርግጠኞች ነበሩ። በዩጎዝላቪያ ጦርነት ሊከሰት አይችልም፥ ሊኖርም አይገባም የሚል ከፍተኛ እምነት ነበራቸው።

    ይሁንና፥ በጥቂት ፅንፈኛ ፓለቲከኞች የተመራው የጥላቻና የማስፈራራት ዘመቻው አሸናፊ ወደሌለው የለየለት ጦርነት ሃገሪቷን ማግዶ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ናዚ/ፋሽስት በአውሮፓ ካስከተለው እልቂት ወዲህ በአህጉሯ ታይቶ የማያውቅ እልቂት፥የሰዎች ጭካኔ፥የዘር ማጥፋትና ማፅዳት በሰፊው ተካሔደ፥ ዩጎዝላቪያም እንደ ሃገር መቆም ተሳናት በሗላም ፈረሰች።

    በዚህ ባጠቃላይ ወደ 11 ዓመት በፈጀ ተከታታይና የተወሳሰበ ግጭት ወደ 2መቶ ሺህ በአብዛኛው ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲሞቱ ተፈረደባቸው። ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿም እስከዛሬ ላልተቋጨ ስደት ተዳረጉ። ሌላም ሌላም ብዙ መከራ ደረሰ።

    Wed, 02 Oct 2019 - 26min